ስፔን ከስዊዘርላንድ ተጠባቂው ጨዋታ።

0
89

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በስዊዘርላንድ ጀኔቫ የ ዩኢኤፍኤ የሴቶች ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ኀያሎቹ ስፔናውያን ከስዊዘርላንድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ቡድኖቹ ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ በስታዲየም ዋንክዶርፍ የሚያደርጉት ጨዋታ ወሳኝ ነው።

ሁለቱም ቡድኖች ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ ከሚያደርጉት ፉክክር ባለፈ የእግር ኳሳቸው ዕድገት ምን ላይ እንደደረሰ የሚያሳዩበት እንደሚኾን ነው የሚጠበቀው።

የዓለም ሻምፒዮናዋ ስፔን አሁን ላይ ያለችበት ደረጃ ከማማው ላይ አሁንም እንዳልወረደች ያሳያል።

ስፔን በምድብ ቢ ያደረገቻቸውን ሦሥት የማጣሪያ ጨዋታዎችን አሸንፋ ሩብ ፍጻሜው ላይ ስትደርስ 14 ግቦችን ከመረብ አዋህዳለች።

በተለይም የቡድኑ ኮከብ ኤስቴር ጎንዛሌዝ እና አሌክሲያ ፑቴላስ ግብ በማስቆጠር እና አመቻችቶ በማቀበል ለቡድኑ ውለታ መዋል ችለዋል።

ስፔን ከዚህ በፊት በቅርቡ ከስዊዘርላንድ ጋር በተገናኘችባቸው ጨዋታዎች በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፏ የዛሬው ጨዋታ ምን ሊኾን እንደሚችል ቢያመላክትም ስዊዘርላንድ አስተናጋጅ ሀገር በመኾኗ ጨዋታው የተለየ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ነው የሚጠበቀው።

አስተናጋጇ ስዊዘርላንድ ወደ ሩብ ፍፃሜ ማለፍ የቻለችበት አጣብቂኝ እና ቡድኑ በምድቡ አራት ጎሎችን ብቻ ማስቆጠሩ ብሎም ከስፔን ጋር በተደረጉ ያለፉ ጨዋታዎች ያስመዘገበው ደካማ ውጤት የዛሬውን ጨዋታ ፈታኝ ሊያደርግበት እንደሚችል ጠቋሚ ነው።

ይሁን እንጂ በአሰልጣኟ ፒያ ሰንድሀጅ የሚመራው የስዊዘርላንድ ቡድን 12ኛ ተጫዋች በኾነው ደጋፊው እየተመራ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ሊገባ የሚችልበት ዕድልም ይኖራል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here