አጫጭር የዝውውር ወሬዎች፦

0
166

ባሕር ዳር: ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ቪክቶር ዮኬሬሽ ለአርሰናል ለመፈረም ለንደን ገብቷል። 63 ሚሊዮን ዩሮ እና ለወደፊት ሊጨመር የሚችል 10 ሚሊዮን ዩሮ አርሰናል ለተጫዋቹ ዝውውር ለስፖርቲንግ ለመክፈል ተስማምቷል።

👉አሊሃንድሮ ጋርናቾ ከአልናስር የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። አርጀንቲናዊ ተጫዋች በቀጣይ በኦልድ ትራፎርድ የመቀየቱ ነገር አጠራጣሪ ነው።

አሠልጣኝ አሞሪም ጋር አለመግባባት ውስጥ የሚገኘው ጋርናቾ በክረምቱ ዝውውር ክለቡን እንደሚለቅ እየተነገረ ነው። የሳዑዲው አልናስርም ጋርናቾን ለማስፈረም ፍላጎቱን አሳይቷል።

ነገር ግን አርጀንቲናዊ የመስመር ተጫዋች ፍላጎቱ በአውሮፓ መቆየት በመኾኑ የአልናስርን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ቴሌግራፍ አስነብቧል።

👉ባየር ሙኒክ ሊሃንድሮ ትሮሳርድን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል። በብሊንድ የመረጃ ምንጭ መሰረት የባቫሪያኑ ክለብ ትሮሳርድ እየተከታተለ ያለው ሊዊስ ዲያዝን ከሊቨርፑል ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት የማይሳካ ከኾነ በሚል ነው።

👉ማንቸስተር ዩናይትድ የቦታፎጎን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጥረት ጀምሯል። አንድሬ ኦናና ጉዳት ማስተናገዱ ዩናይትድ አዲስ ግብ ጠባቂ የማግኘት ፍላጎቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎታል።

ሰን የመረጃ ምንጭ እንደ ጻፈው ዮሃን ቪክቶር ከቦታፎጎ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ለመዛወር አኹን የተሻለ እድል አለው።

👉ሊቨርፑል የሊፕዚንጉን ቤንጃሚ ሲሴኮን ጉዳይ እየተከታተለ ነው። በአርሰናል ሲፈለግ የነበረው ሲሴኮ አርሰናል ዩክሬሽን በመምረጡ ወደ ለንደኑ ክለብ እንደማይዘዋወር እውን ኾኗል።

ይህን ተከትሎ ሊቨርፑል አጥቂውን ለማግኘት እየገፋ ነው።

👉የብራይተኑ ኢይቫን ፈርጉሰን ሮማን ለመቀላቀል ተስማምቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here