ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በፊፋ ክለቦች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ የእንግሊዙን ቼልሲ ከብራዚሉ ፍሉሚኔንሴ በሜትላይፍ ስታዲየም የሚያደርጉት የዛሬው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ፍሉሚኔንሴ እና ቼልሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የሚገናኙት። ሁለቱም ቡድኖች ግማሽ ፍጻሜው ላይ ለመድረስ ጠንካራ ፉክክር አድርገዋል። ፍሉሚኔንሴ በእስካኹን የክለቦች የዓለም ዋንጫ ጉዞው ሽንፈት አልገጠመውም።
በጥሎ ማለፉ ኢንተር ሚላንን 2ለ0 በማሸነፍ እና በሩብ ፍፃሜው ደግሞ አል ሂላልን 2ለ1 በማሸነፍ ነው ለግማሽ ፍፃሜው መድረስ የቻለው። የቀድሞው የቼልሲ አምበል ትያጎ ሲልቫ የድሮ ክለቡ ቼልሲን ይገጥማል።
የኮንፈረንስ ሊግ አሸናፊው ቼልሲ በዚህ ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥንካሬውን እያሳየ ነው።
ከምድቡ ሁለተኛ ኾኖ 16ቱ ውስጥ የገባው ቼልሲ ቤንፊካን 4ለ1 በማሸነፍ እና ከዚያም ፓልሜራስን 2ለ1 አሸንፎ ለግማሽ ፍጻሜው በቅቷል።
የዛሬው ጨዋታ አሸናፊ ከሪያል ማድሪድ እና ፒኤስጂ አሸናፊ ጋር ለዋንጫ ይፋለማል።
ጨዋታ ምሽት አራት ሰዓት ይደረጋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን