ባሕር ዳር: ግንቦት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዩኤፍኤ ኮንፈረንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ፣ ቼልሲ ሪያል ቤቲስን 4 ለ 1 በኾነ ውጤት አሸንፎ ዋንጫውን አንስቷል።
የቸልሲን ግቦች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ፣ኒኮላስ ጃክሰን ፣ጄዶን ሳንቾ እና ካይሴዶ አስቆጥረዋል።
ቼልሲ በዛሬው ድሉ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ አራቱንም የአውሮፓ ዋንጫዎች ያነሳ ብቸኛው ቡድን ለመኾን ችሏል፡፡
ሪያል ቤቲስ በበኩሉ በአውሮፖ ውድድሮች በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን