የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ አዲሱ የባየር ሊቨርኩሰን አሠልጣኝ ኾነዋል። ሊቨርኩሰን ባለፉት ዓመታት በዣቪ አሎንሶ ሲሠለጥን ቆይቷል።
አሎንሶ ሪያል ማድሪድን ለማሠልጥን መስማማቱን ተከትሎ ተተኪውን ሲያፈላልግ የነበረው የጀርመኑ ክለብ ቴንሃግን ምርጫው አድርጓል። ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ክለቡን እንዲሚያሠለጥኑም የጎል ዶት ኮም መረጃ ያሳያል።
ኔዘርላንዳዊ አሠልጣኝ በማንቸስተር ዩናይትድ የስንብት ደብዳቤ ከደረሳቸው በኋላ ያለሥራ ቆይተዋል።