ባሕር ዳር: ግንቦት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ቶተንሀም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ኾኗል። የቶተንሀምን ወሳኝ የማሸነፊያ ግብ ብሬናን ጆንሰን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የለንደኑ ክለብ ቶተንሀም በታሪኩ ሦስተኛውን የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ ችሏል።
አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ክለቡን በተረከቡ ሁለተኛ ዓመታቸው ዋንጫ የማሸነፍ ሪከርዳቸውን አስቀጥለዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአውሮፓ መድረክ የማይሳተፍ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!