በሴቶች የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ደብረ ብርሃን ከተማ አሸናፊ ኾነ።

0
79

ደሴ: ግንቦት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዘጠነኛው የመላ አማራ ጨዋታዎች በሴቶች እግር ኳስ ጨዋታ ደብረ ብርሃን ከተማ ደሴ ከተማን 1 ለ 0 በመርታት የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ኾኗል። ደሴ ከተማ ደግሞ 2ኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ነው።

የባሕር ዳር ከተማ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን ደግሞ ሦስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ መኾን ችሏል። በወንዶች ለደረጃ በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ደግሞ ደቡብ ወሎ ዞን ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አሥተዳደርን 1 ለ 0 በመርታት 3ኛ ደረጃን በመያዝ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ኾኗል።

የዘጠነኛው የመላው አማራ ጨዋታዎች የመዝጊያ መርሐ ግብር በደሴ ሆጤ ስታድየም ሐሙስ ግንቦት 14/2017 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ሲኾን በወንዶች የፍፃሜ ጨዋታ ሰሜን ወሎ ዞን ከደሴ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ዘጋቢ:-ጀማል ይማም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here