በጅምናስቲክ ውድድር የሰሜን ሽዋ ዞን አሸናፊ ኾነ።

0
109

ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዘጠነኛው የመላው አማራ ስፖርታዊ ጨዋታ እንደቀጠለ ነው። በጅምናስቲክ ውድድር ሰሜን ሽዋ ዞን በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ ኾኗል። በውድድሩ አራት ዞኖች የተሳተፉ ሲኾን ሰሜን ሽዋ ዞን አምስት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት አሸናፊ ኾኗል።

ደቡብ ጎንደር አራት የወርቅ፣ ሰባት የብር እና አራት የነሐስ ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ የሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ደግሞ አራት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና አምስት የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘት በሦሥተኛነት ውድድሩን ማጠናቀቁን ከክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

በሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here