የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ እጩዎች ይፋ ኾኑ።

0
118

ባሕር ዳር: ግንቦት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊጠናቀቅ ሁለት ጨዋታዎች ብቻ ይቀራሉ። የውድድር ዓመቱ ሊቨርፑልን አሸናፊ አድርጓል። ሳውዝአፕተን፣ ሌስተር እና ኢፕሲዎችን በመጡበት ዓመት ወደታች መልሷል። ቀሪ ሁለት ጨዋታዎችም የአውሮፓ መድረክ ተሳታፊ ቡድኖችን ይለያሉ።

ሊጉ በዓመቱ በግለሰብ ደረጃ ምርጥ ብቃት ካሳዩ ተጫዋቾች እና አሠልጣኞች መካከል የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች እና አሠልጣኝ ይመረጣል። በዚህ መሠረት ለምርጥ ተጫዋችነት ከዋንጫ ባለቤቱ ሊቨርፑል ሦስት ተጫዋቾች እጩ ኾነዋል። ሞ ሳላህ፣ ቨርጅል ቫንዳይክ እና ሪያን ግራን ቫንብራክ ደግሞ ተጫዋቾቹ ናቸው።

የኒውካስትሉ አሌክሳንደር ኢዛክ፣ የአርሰናሉ ደክለን ራይስ፣ የብሬንት ፎርዱ ብራያን ሙቦሞ፣ የኖቲንግሃሞቹ ክሪስውድ እና ጊብስ ዋይት ሌሎች እጩዎች ናቸው። በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ቡድናቸውን ስኬታማ በማድረግ የተሻሉ አሠልጣኞች ለዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝነት እጩ ኾነዋል።

የሊቨርፑሉ አሠልጣኝ አርኒ ስሎት፣ የብሬንትፎርዱ ቶማስ ፍራንኬ፣ የኒውካስትሉ ኤዲ ሀው፣ የኖቲንግሃሙ ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶ እና የዎልብሱ ቪቶር ፔሬራ ለዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝነት እጩ ኾነዋል።

ዘጋቢ፦ አስማማው አማረ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here