የጣና ሞገዶቹ ሁለተኛ ደረጃን ለመረከብ በማሰብ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይጫወታሉ።

0
92

ባሕር ዳር: ሚያዚያ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ዛሬ ባሕር ዳር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ወሳኝ ጨዋታውን ያደርጋል። በደረጃ ሰንጠረዡ ሦስተኛ ላይ የሚገኙት የጣና ሞገዶቹ 12ኛ ደረጃ ላይ ካለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ነው የሚፋለሙት።

ባለፈው ጨዋታ ድል የቀናቸው የጣና ሞገዶቹ የውድድር ዓመቱን በጥሩ ኹኔታ ለመጨረስ እየጣሩ ነው። ምንም እንኳን የማጥቃት አጨዋወታቸው መሻሻል ቢያሳይም፣ በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ተመሳሳይ ብቃት ማሳየት ላይ ክፍተቶች ተስተውለዋል። በዚህ ሳምንት ለጣና ሞገዶቹ እንደ እድል የሚታየው ሁሉም ተጫዋቾች ለዚህ ወሳኝ ጨዋታ ዝግጁ መኾናቸው ነው።

በሌላ በኩል ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎቹ ሁለቱን ተሸንፎ አንዱን በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ቡድኑ አሁንም ከመሸነፍ ሥነ ልቦና እንዳልወጣ ያሳያል። ቡድኑ የአጥቂ ክፍሉ ባለፉት ጨዋታዎች እንደታየው ደካማ የሚባል ነው፤ ይህም የባሕር ዳር ከተማን ተከላካዮች አልፈው ግብ ለማስቆጠር አዳጋች ሊኾንባቸው እንደሚችል ነው የሚጠበቀው።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአብዛኛው በመከላከል ላይ ያተኮረ የጨዋታ ስልት ይዞ ወደ ሜዳ ሊገባ እንደሚችል ይጠበቃል። ሁለቱ ቡድኖች በፕሪምየር ሊጉ ሦስት ጊዜ ተገናኝተው ባሕር ዳር ከተማ ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ጊዜ አሸንፏል።

በዚህም ግንኙነት ባሕር ዳር ከተማ በአጠቃላይ አምስት ግቦችን ሲያስቆጥር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሦስት ግቦችን አስቆጥሯል። ጨዋታውም ቀን 9፡00 ይካሄዳል።

በሌላ የዛሬ ጨዋታ 12:00 ሰዓት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቻል ይጫወታሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here