ፋሲል ከነማ ከሽንፈት ለማገገም ከሀድያ ጋር ይጫወታል።

0
92

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአራት ነጥቦች የሚለያዩት ፋሲል ከነማ እና ሀድያ ሆሳዕና ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ጨዋታ 9፡00 ላይ ይገናኛሉ።

በ33 ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት ከደረሰበት በኋላ ወደ ድል ለመመለስ ዛሬ ጠንክሮ ይጫወታል ተብሎ ነው የሚገመተው።

ቡድኑ ካለበት ደረጃ አንጻር ነጥቡ አኹንም አሳሳቢ በመኾኑ አጥቂ ክፍሉን አጠናክሮ ግብ ለማስቆጠር እንደሚገባ ተስፋ ተደርጎበታል።

በ37 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ሀድያ ሆሳዕና በበኩሉ ወላይታ ድቻን በማሸነፍ የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።

ምንም እንኳን ቡድኑ ከዚህ ቀደም ጥሩ ጊዜ ቢያሳልፍም በቅርብ ሳምንታት የውጤት መዋዠቅ ገጥሞታል።

ወላይታ ድቻ ላይ ባለፉት ጨዋታዎች ላይ የታየው የተሳካ የመልሶ ማጥቃት የአጨዋወት ስልት ዛሬ ሜዳ ላይ እንደሚደገም ነው የሚጠበቀው።

ሁለቱ ቡድኖች ቀደም ሲል ዘጠኝ ጊዜ ተገናኝተው አራት ጊዜ አቻ ሲለያዩ ፋሲል ከነማ አራቱን አሸንፏል። ሀድያ ሆሳዕና አንድ ጊዜ አሸንፏል።

በሌላ የዛሬ ጨዋታ 12፡00 ላይ መቀለ 70 እንደርታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here