ተጠባቂው ተንቅንቅ በኤምሬትስ!

0
110

ባሕር ዳር:ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይካሄዳሉ። ዛሬ አርሰናል በሜዳው ከፓሪስ ሴንት ዠርሜ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በእግር ኳስ አፋቃሪያን ዘንድ በጉጉት ይጠበቃል። ፒኤስጅ በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ብዙ ጊዜ የተገናኘው እና ያላሸነፈው ቡድን አርሰናል ነው። ቡድኖቹ ከዚህ በፊት በተገናኙባቸው አምስት ጨዋታዎች አርሰናል አልተሸነፈም።

አርሰናል በዚህ የውድድር ዓመት ቀደም ሲል በኤምሬትስ ስታዲዮም በተካሄደው የሊግ ምድብ ጨዋታ 2ለ0 በኾነ ውጤት ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን አሸንፏል። አንድ የእንግሊዝ ቡድን ብቻ በአንድ የውድድር ዓመት ሁለት ጊዜ ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን አሸንፏል፤ ይህም ማንቸስተር ሲቲ በ2020/21 የውድድሩ ግማሽ ፍጻሜ ላይ ነው።

ፓሪስ ሴንት ዠርሜን ካለፉት ስድስት ከሜዳው ውጭ ባደረጋቸው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች አምስቱን ተሸንፏል፤ ማንቸስተር ሲቲ ሁለት ጊዜ፣ አርሰናል፣ ኒውካስትል እና አስቶን ቪላ ናቸው ያሸነፉት። ይህ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ሁለት ስፔናዊ አሠልጣኞች ሚኬል አርቴታ ከአርሰናል እና ሉዊስ ኤንሪኬ ከፓሪስ ሴንት ዠርሜን የሚፋለሙበት ሦስተኛው ይኾናል።

ከዚህ ቀደም በ2001/02 ከባርሴሎና፣ ከሪያል ማድሪድ እና በ2014/15 ከባየር ሙኒክ እና ከባርሴሎና ተገናኝተዋል። አርሰናል በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ያለፉትን ስምንት ጨዋታዎች አልተሸነፈም። በሻምፒዮንስ ሊጉ ይህ በአንድ የውድድር ዓመት ያስመዘገበው ሁለተኛው ረጅሙ ያለመሸነፍ ጉዞ ነው።

ከዚህ ቀደም በ2005/06 12 ጨዋታዎችን ያለሽንፈት ማጠናቀቁ ይታወሳል፤ በዚያው ዓመትም ለውድድሩ ፍጻሜ ደርሶ በባርሴሎና መሸነፉ ይታወሳል። የዛሬው ጨዋታ ከታሪካዊ ግንኙነታቸው አኳያ የአርሰናል እና የፓሪስ ሴንት ዠርሜን የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረትን የሚስብ ነው።

የአርሰናል ያለመሸነፍ ጉዞ እና በውድድሩ ያስመዘገበው ውጤት እንዲኹም የፓሪስ ሴንት ዠርሜን ከእንግሊዝ ቡድኖች ጋር ያለው ደካማ የሜዳ ውጭ ውጤት ጨዋታውን የበለጠ ተጠባቂ ያደርገዋል። በተጨማሪም ሁለቱ ስፔናዊ አሠልጣኞች ሚኬል አርቴታ እና ሉዊስ ኤንሪኬ የሚያደርጉት ፍልሚያ ለጨዋታው ሌላ ገጽታ ይጨምራል።

የቡካዮ ሳካ እና የኡስማን ዴምቤሌ ፉክክር የደጋፊዎችን ቀልብ መሳቡ ቀልብ ስቧል። ይህ የሁለቱ ቡድኖች ትንቅንቅ ክፍል አንድ በኤምሬትስ ምሽት 4፡00 ሰዓት ይካሄዳል። ክፍል ሁለት ሳምንት ፈረንሳይ ላይ ይጠበቃል።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here