ባሕር ዳር: ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መድፈኞቹ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ባደረጓቸው ያለፉት አምስት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ድልን አስመዝግበዋል።
ምንም እንኳን ክሪስታል ፓላስ ከዚህ በፊት በአርሰናል ሜዳ ጥሩ ባይኾንም በለንደን ደርቢዎች የተሻለ ብቃት እያሳየ ይገኛል።
ኾኖም ግን በአጠቃላይ የአርሰናል የበላይነት እና በሜዳው ያለው ጥንካሬ ጨዋታውን ለመድፈኞቹ ብዙም አስቸጋሪ እንደማያደርገው ይጠበቃል።
በተለይም እንደ ማርቲኔሊ እና ራይስ ያሉ ተጫዋቾች ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳዩ በመኾኑ አርሰናል ጨዋታውን የማሸነፍ ዕድሉ ሰፊ ነው።
በሌላ በኩል የክሪስታል ፓላሱ አጥቂ ማቴታ በለንደን ቡድኖች ላይ ግብ የሚያስቆጥር ተጫዋች ቢኾንም በኤሚሬትስ ስታዲየም የአርሰናልን የተከላካይ መስመር ሰብሮ መግባት ይችል ይኾን? የሚለው ይጠበቃል።
በፕሪምየር ሊጉ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ አጥብቆ የሚፈልገውን ሦስት ነጥብ አሳክቷል።
የሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ለማጎኘት እየታተሩ ያሉት ሲቲና አስቶንቪላ ያደረጉት ይህ ጨዋታ በማንቸስተር ሲቲ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ድሉን ተከትሎ የጋርዲዮላው ቡድን ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን