ባሕር ዳር:ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ በተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቷቸዋል።
ኢትዮጵያ መድን ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2ለ0 በማሸነፍ ነው መሪነቱን ያጠናከረው። ሁለቱንም የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ አበራ አስቆጥሯል።
ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በሀዋሳ ከተማ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች አሊ ሱሌማን ሲያስቆጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ሱሌማን ሀሚድ አስቆጥሯል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን