ባሕር ዳር:ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፊታችን እሑድ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት በውድድሩ እንደማይሳተፍ አስታውቋል።
አለመሳተፉ ቅር ቢያሰኘውም ለማገገም ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ መኾኑን ገልጿል። ውድድሩን እየተጠባበቅሁ ነበር፤ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ በዝግጅቴ ወቅት ጉዳት አጋጥሞኛል፤ እናም በዚህ ዓመት መሳተፍ አልችልም ብሏል።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በመላው ዓለም የሚገኙ ለአድናቂዎቹ ለሳዩት ድጋፍ ምሥጋናውን አቅርቧል።
ወደፊት በሚደረጉ ውድድሮች ላይ እንደምቀላቀላችሁ ተስፋ አደርጋለው ያለው አትሌቱ ይህንንም በጉጉት እንደሚጠብቅ ነው የተናገረው።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልእክት በዚህ ታላቅ ውድድር ለሚሳተፉት አትሌቶች መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን