ባሕር ዳር:ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ 26ኛ ሳምንት ከሰዓት በኋላ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። ባሕር ዳር ከተማን ከመቐለ 70 እንደርታ ያገናኘው ጨዋታ በሞገዶቹ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
የጣና ሞገዶቹ 4 ለ 1 በኾነ ውጤት ነው ማሸነፍ የቻሉት።
ግቦቹን ቸርነት ጉግሳ እና አቤል ማሙሽ አስቆጥረዋል።
ለመቐለ 70 እንደርታ ደግሞ ብቸኛ ግቧን አሸናፊ ሀፍቱ አስቆጥሯል።
በሌላ በኩል ፋሲል ከነማ በድሬዳዋ ከተማ ተሸንፏል። ግቧን ለድሬዳዋ ከተማ አስራት ቱንጆ አስቆጥሯል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን