አርሰናል እና ኢንተር ሚላን ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ።

0
156

ባሕር ዳር ሚያዚያ: 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 አሸንፏል። በሌላ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ከባየር ሙኒክ 2 ለ 2 ተለያይተዋል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ቡካዩ ሳካ እና ጋብሬል ማርቲኔሊ ሲያስቆጥሩ ለሪያል ማድሪድ ቪንሰስ ጁኒየር ከመረብ አሳርፏል።

የኢንተር ሚላንን ግቦች ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ፓቫርድ ሲያስቆጥሩ ለባየር ሙኒክ ሀሪ ኬን እና ዳየር ከመረብ አሳርፈዋል።

አርሰናል ሪያል ማድሪድን በድምር ውጤት 5 ለ 1 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል። ኢንተር ሚላን ደግሞ ጨዋታውን በድምር ውጤት 4 ለ 3 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

አርሰናል በግማሽ ፍፃሜው የፈረንሳዩን ሻምፒዮን ክለብ ፒኤስጂን ሲገጥም ኢንተር ሚላን ደግሞ ከባርሴሎና ጋር የሚገናኝ ይኾናል።

በታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here