በጉጉት የሚጠበቁት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች።

0
197

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ አርሰናል ሪያል ማድሪድን 3ለ0 በኾነ ውጤት በማሸነፍ አስደናቂ ብቃት ማሳየቱ ይታወሳል። ይህ ውጤት መድፈኞቹ በአውሮፓ ዋንጫ ከሪያል ማድሪድ ጋር ባደረጓቸው ሦስት ጨዋታዎች ሳይሸነፉ እንዲቆዩ ከማድረጉም በላይ ምንም ግብ ሳይቆጠርባቸው እንዲወጡ አስችሏቸዋል።

በተጨማሪም በኤምሬትስ ስታዲየም የተሸነፈው ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር በሦስት እና ከዚያ በላይ በኾነ ግብ ሲሸነፉ ለአምስተኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ከአራት አጋጣሚዎች ሦስቱ ላይ ከውድድሩ ውጭ ኾኖም ነበር። ብቸኛው የተለየ ኹኔታ በ1975/76 በደርቢ ካውንቲ ላይ ያስመዘገቡት አስደናቂ የ6ለ5 አጠቃላይ ድል ነበር። ይህም የመጀመሪያውን ዙር ጨዋታ 4ለ1 ተሸንፈው በሁለተኛው ዙር 5ለ1 ያሸነፉበት አጋጣሚ ነው።

አርሰናል በዚህ የውድድር ዘመን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በአማካይ 2 ነጥብ 55 ግቦችን ያስቆጠረ ሲኾን በአንድ ጨዋታ ደግሞ 0 ነጥብ 55 ግቦች ተቆጥረውበታል። በአጠቃላይ 28 ግብ አስቆጥሮ 6 ተቆጥሮበታል።

ይህም በ2010/11 ካስቆጠረው 2 ነጥብ 63 እና በ2005/06 ከተቆጠሰበት 0 ነጥብ 31 ጎሎች በመከተል በውድድሩ ያስመዘገበው ሁለተኛው ምርጥ አማካይ ነው።

የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ኪሊያን ምባፔ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከእንግሊዝ ቡድኖች ጋር ባደረጋቸው ስምንት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ስምንት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል ይህም በአራት የሜዳው ጨዋታዎች አምስት ጎሎችን ያካትታል።

በአኹኑ ወቅት 28 ግቦች እና 21 አሲስቶች ያሉት ቪኒሲየስ ጁኒየር በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 50 የግብ ተሳትፎዎችን የደረሰ አራተኛው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ሊኾን የሚችልበት ዕድል ያለው ሲኾን ይህም ከክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ካሪም ቤንዜማ እና ራውል ቀጥሎ ማለት ነው።

በዚህ ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር ላይ ማይልስ ሌዊስ ስኬሊ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለግብ ያቀበለ ሦስተኛው እንግሊዛዊ ታዳጊ ኾኗል።

እነዚህ ሦስት ተጫዋቾች ሁሉም ለአርሰናል ሲጫወቱ ነው ይህንን ስኬት ያስመዘገቡት። ቴዎ ዋልኮት በ2008 ከኤሲ ሚላን እና ሊቨርፑል ጋር ሲጫዎቱ፣ አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሊን በ2012 ከኤሲ ሚላን ጋር እና ማይልስ ሌዊስ ስኬሊ በ2025 ከሪያል ማድሪድ ጋር ሲጫዎቱ ነው።

ከእነዚህ እና መሠል ታሪካዊ መረጃዎች በመነሳት አርሰናል በሳምንቱ መጨረሻ በሳንቲያጎ በርናባው በሚደረገው የሁለተኛው ዙር ጨዋታ ሪያል ማድሪድን ደግሞ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ከፍተኛ ዕድል እንዳለው መገመት ይቻላል።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሌላው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ ዛሬ ምሽት 4:00 ኢንተር ሚላን ባየር ሙኒክን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።

ሁለቱ ቡድኖች በውድድሩ ታሪክ የረጅም ጊዜ ፉክክር ያላቸው ናቸው። ያለፉት ስድስት ጨዋታዎቻቸውም እያንዳንዳቸው ሦስት ጊዜ በማሸነፍ እኩል ናቸው።

ባየር ሙኒክ በአውሮፓ ውድድሮች በኢንተር ሜዳ አራት ጨዋታዎችን ያደረገ ሲኾን በሁሉም አሸንፏል።

በተለይም በሻምፒዮንስ ሊግ ባደረጋቸው ሦስት የሜዳ ውጭ ጨዋታዎች ላይ ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ማሸነፍ ችሏል።

ኢንተር ሚላን በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ካሸነፈባቸው 23 የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች 21 ጊዜ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል።

ኢንተር በሜዳው በሻምፒዮንስ ሊግ ላለፉት 14 ጨዋታዎች ሳይሸነፍ ቆይቷል። ይህ በአኹኑ ጊዜ በውድድሩ ረጅሙ ሪከርድ ሲኾን ኢንተር በመጀመሪያው ጨዋታ ባየር ሙኒክን በአሊያንዝ አሬና 22 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ክብረ ወሰን በማቆሙ የተገኘ ነው።

የኢንተር ሚላኑ ኮከብ ላውታሮ ማርቲኔዝ ባለፉት አራት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር የቻለ ሲኾን በአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው የኢንተር ተጫዋች ለመኾንም ዛሬ ይተጋል።

የኢንተር ሚላን ቤንጃሚን ፓቫርድ 50ኛውን የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውን ሊያደርግ ይችላል አሁን ላይ 49 ጨዋታዎችን አድርጓል።

እስካኹን ካደረጋቸው 49 ጨዋታዎች 40 ድሎችን ያስመዘገበ ሲኾን ይህም በውድድሩ ታሪክ በመጀመሪያዎቹ 50 ጨዋታዎች ብዙ ድሎችን ያስመዘገበ ተጫዋች ያደርገዋል።

በአጠቃላይ ዛሬ ምሽት በሳን ሲሮ የሚደረገው ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚታይበት ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here