ባሕር ዳር: ሚያዝያ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ “ለ ” ን 38 ነጥብ በመሰብሰብ ከነገሌ አርሲ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ በሁለተኛነት የተቀመጠው ደሴ ከተማ (ቅኝቶቹ) ስድስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ሻሸመኔ ከተማ ጋር እየተጫወተ ነው።
ደሴ ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ መግባት የሚያስችለውን ዕድል ይበልጥ ለማስፋት ይህ ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይለዋል።
ደሴ ከተማ ሻሸመኔ ከተማን ከአሸነፈ ምድቡን መምራት ያስችላቸዋል።
ደሴዎች አቻ ቢለያዩም ነገሌ አርሲ እሁድ ከሀላባ ከተማ ጋር እስኪጫዎት ድረስ በግብ ክፍያ በልጠው የሊጉ መሪ ያደርጋቸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!