መሀመድ ሳላህ በሊቨርፑል የውሉ የመጨረሻ ዓመት ላይ ይገኛል። በቀዮቹ ቤት ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ያለው ይህ ግብጻዊ ዓመቱ በሊቨርፑል የመጨረሻው እንደሚኾን በተደጋጋሚ ሲናገር ተደምጧል።
ይህን ተከትሎ የሳውዲ ክለቦች በገፍተኛ ገንዘብ ተጫዋቹን ለመውሰድ በጉጉት እየጠበቁ ነበር።
ነገር ግን ቢቢሲ በስፖርት ገጹ ባወጣው መረጃ መሰረት ሳላህ በሊቨርፑል እንደጎርግሮሳውያን እስከ 2027 ለመቆየት ተስማምቷል።