ጫና የበረታባቸው አንቾሎቲ!

0
118

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ እግር ኳስ ውጤታማ ተብለው ከሚጠሩ አሠልጣኞች አንዱ ናቸው ካርሎ አንቾሎቲ። ጣሊያናው አሠልጣኝ በተለይ በጣሊያኑ ኤሲሚላን እና በስፔኑ ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውጤታማነት አንቱ ተብለዋል።

በጣሊያን ሴሪኤ፣ በስፔን ላሊጋ እና በፈረንሳዩ ሊግ አንደም ተደጋጋሚ ስኬታማ ሰው ናቸው።

ነገር ግን እኝህ ውጤታማ አሠልጣኝ አኹን ወንበራቸው እየተነቃነቀ ነው። ሪያል ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊግ በአርሰናል 3ለ0 ከተሸነፈ በኋላ የካርሎ አንቸሎቲ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ ወድቋል።

በላሊጋም ኾነ በሻምፒዮንስ ሊግ ውጤታቸው ካልተሻሻለ አሠልጣኙ ከነጮቹ ቤት ሊሰናበቱ እንደሚችል እየተነገረ ነው።

ሪያልማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ከቀናት በፊት በአርሰናል 3ለ0 መሸነፉ በአንቾሎቲ ላይ ጥያቄ አስነስቶባቸዋል።

በቀጣይ ሳምንት በሜዳው በሚያደረገው የመልስ ጨዋታ ማድሪድ ውጤቱን ቀልብሶ ወደ ቀጣይ ዙር የማያልፍ ከኾነም ጣሊያናዊ አሠልጣኝ የማድሪድ ቆይታ ሊያጥር እንደሚችል ጎል የመረጃ ምንጭ አስነብቧል።

የባየር ሌቨርኩሰኑ አሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ቀጣዩ የሪያል ማድሪድ አሠልጣኝ ሊኾኑ እንደሚችሉም መረጃዎች አብረው እየወጡ ነው።

ሪያል ማድሪድ በቻምፒዮንስ ሊጉ በሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በሰፊ ግብ ከመሸነፉ በተጨማሪ በላሊጋው በባርሴሎና በአራት ነጥብ መበለጡ የጣሊያናዊ አሠልጣኝ የመሰናበት ዜና አበርትቶታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here