በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ ባሕር ዳር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

0
86

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ 24ኛ ሳምንት ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ይካሄዳል። በ34 ነጥብ 4ኛ ደረጃ የሚገኘው ባሕርዳር ከተማ እና በ36 ነጥብ 3ኛ ደረጃ የሚገኘውን ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ሁለቱም ቡድኖች በደረጃ ሠንጠረዡ የተሻለ ቦታ ለመያዝ ይፋለማሉ፡፡ ዛሬ የሚያስመዘግቡት ውጤት በዋንጫ ፉክክሩ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። በተሻለ አቋም ላይ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች የዛሬ ጨዋታቸውን እንዲጠበቅ አድርጎታል።

በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለው ታሪካዊ ግንኙነት ሲፈተሽ የበላይነቱን ባሕር ዳር ከተማ ይወስዳል። አምስት ጊዜ በማሸነፍ ከኢትዮጵያ ቡና በሁለት ድሎች ብልጫ አለው። አምስት ጨዋታዎችም በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል።

ጨዋታው ተጠባቂ ከመኾኑ ጋር ተያይዞ አሠልጣኞች ለዛሬው ፍልሚያ የተለየ ስልት ሊጠቀሙ ይችላሉ።

በሌላ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይገናኛሉ።

ከዚህ ቀደም በሁለቱ ቡድኖች መካከል የተደረጉ ጨዋታዎችን ስንመለከት የጨዋታ የበላይነትን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይዟል። አራት ጊዜ በማሸነፍ ከአርባ ምንጭ ከተማ በሦስት ድሎች በልጦ ተቀምጧል። ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል።

የሁለቱም ቡድኖች አሠልጣኞች ለዚህ ወሳኝ ጨዋታ የተለየ ስልት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ይጠበቃል።

ዛሬ የሚደረገው ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚኖረው የሚጠበቅ ሲኾን ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ የተሻለ ቦታ ለመያዝ ከፍ ያለ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡

የኢትዮጵያን ፕሪምዬር ሊግ ኢትዮጵያ መድን በ45 ነጥቦች እየመራው ነው። ወላይታ ድቻ ደግሞ በ37 ነጥብ ይከተላል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here