ባርሴሎና እና ፒኤስጂ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ።

0
96

ሚያዚያ: 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ የስፔኑ ባርሴሎና የጀርመኑን ዶርትመንድ 4 ለ 0፤ የፈረንሳዩ ፒኤስጂ የእንግሊዙን አስቶን ቪላ 3 ለ1 አሸንፈዋል። የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ሌዋንዶውስኪ 2፣ ላሚን ያማል እና ራፊና አስቆጥረዋል።

ፒኤስጂን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ዱዌ ፣ ሜንዴዝ እና ቅቫራስኬሊያ ሲያስቆጥሩ ለአስቶን ቪላ ሮጀርስ ከመረብ አሳርፏል። ራፊና በአንድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ዓመት ለባርሴሎና 19 የግብ ተሳትፎ በማድረግ የሊዮኔል ሜሲን ሪከርድ ተጋርቷል።

ሌዋንዶውስኪ በሻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ በሦስት የተለያዩ ክለቦች ከ10 በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው ተጨዋች መኾን ችሏል። ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በውድድር ዘመኑ በሁሉም ውድድሮች 40 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ራፊና በውድድር ዘመኑ 12 የሻምፒየንስ ሊግ ግቦችን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል። የመልሱ ጨዋታ በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here