ዛሬ ተጠባቂ የቻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
122

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ሲቀጥል የስፔኑ ባርሴሎና የጀርመኑን ቦሩሲያ ዶርትሙንድን በሜዳው ያስተናግዳል። ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ የሚካሄደውን ጨዋታ የእግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት ይጠብቁታል። ባርሴሎና በአሁኑ የቻምፒዮንስ ሊግ የውድድር ዘመን ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።

በተለይም በሜዳው በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች 14 ጎሎችን በማስቆጠር የተሻለ ብቃት አሳይቷል። የቅርብ ጊዜ ውጤቶቹ በአብዛኛው የተሻሉ በመኾናቸው ለዚህ ጨዋታ የተሻለ ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት ይዘው ይገባሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በሌላ በኩል ቦሩሲያ ዶርትሙንድ በቻምፒዮንስ ሊጉ በአጠቃላይ 28 ጎሎችን አስቆጥሯል። የቅርብ ጊዜ ውጤቶቹ ያን ያህል የሚያኮሩ አይደሉም። ምንም እንኳን አንዳንድ ጥሩ ድሎችን ቢያስመዘግብም።

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በሁሉም ውድድሮች ሦስት ጊዜ ተገናኝተዋል። በዚህም ባርሴሎና ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል። በሌላ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት የፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጅ የእንግሊዙን ተፎካካሪ አስቶን ቪላን በሜዳው ያስተናግዳል።

ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን በየትኛውም ውድድር ተገናኝተው አያውቁም። ስለዚህ ይህ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙበት ይኾናል። ሁለቱም ቡድኖች በቅርብ ጊዜያት ጥሩ ውጤቶችን እያስመዘገቡ በመኾናቸው ይህ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚኖረው ይጠበቃል።

ፒኤስጂ በደጋፊዎቹ ፊት መጫወቱ የተወሰነ ጥቅም ሊሰጠው ቢችልም አስቶን ቪላም ከሜዳው ውጭ ጥሩ ውጤቶችን ማስመዝገቡ ለዚህ ጨዋታ በልበ ሙሉነት እንዲገባ ያደርገዋል።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here