ባሕር ዳር: መጋቢት 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረገውን የሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 በኾነ ውጤት አሸንፏል።
የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ዴክላን ራይስ 2 እና ሚኬል ሜሪኖ አስቆጥረዋል።
በጨዋታው ዴክላን ራይስ ሁለት የቅጣት ምት ግቦችን ሲያስቆጥር ሪያል ማድሪድ በ17 ደቂቃዎች ሦስት ግቦችን አስተናግዷል።
በጨዋታው ኤድዋርዶ ካማቪንጋ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
በሌላ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ከባየር ሙኒክ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 1 በኾነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የኢንተር ሚላንን ግብ ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ፍራቴሲ ሲያስቆጥሩ ለባየር ሙኒክ ቶማስ ሙለር ከመረብ አሳርፏል።
የመልስ ጨዋታዎች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ የሚካሄዱ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!