ፍኖተ ሰላም: መጋቢት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር የመላ ጨዋታዎች ስፖርታዊ ውድድር መካሄድ ጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዮናስ ሞላ ስፓርት ፍቅር፣ ሰላም እና አንድነት እንዲጎለብት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል። ስፖርታዊ ውድድሩ ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል በላይ ተቀዛቅዞ የነበረውን የስፓርት ዘርፍ በማነቃቃት የከተማውን ገጽታ በመቀየር ሚናው የጎላ መኾኑን ተናግረዋል።
በተለይም የስፓርታዊ ውድድሩ ወጣቶች ከአልባሌ ቦታዎች እንዲርቁ እና የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከር እንደሚረዳ ነው የገለጹት።
የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ብንያም ጌጡ የመላ ስፓርታዊ ጨዋታዎች ውድድር በአራት ቀበሌዎች መካከል በሰባት የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ መኾኑን ገልጸዋል።
በቀጣይ ለሚከናወኑ ዞናዊ እና ክልላዊ ጨዋታዎች ተወዳዳሪዎችን ለመመልመል እና በስፖርተኞች ዘንድ መነቃቃት እንዲፈጠር እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!