ባሕር ዳር፡ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባርሳው ራፊንሃ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሳይሰለፍ ከቆየ በኋላ ነገ ጨዋታውን በቋሚ ተሰላፊነት ይጀምራል ተብሏል።
✍️ኤንድሪክ ዛሬ ማታ ሪያል ማድሪድ ከሪያል ሶሲዳድ ጋር በሚደረገው ጨዋታ የመጀመሪያ ተሰላፊ እንደሚኾን ይጠበቃል።
✍️ኤርሊንግ ሃላንድ በቁርጭምጭሚት ጉዳት ከ5 እስከ 7 ሳምንታት እንደማይሰለፍ አሠልጣኙ ጋርዲዮላ አረጋገጡ።
✍️በሪያል ማድሪድ ቤት ደስተኛ መሆኑን የተናገረው ጁድ ቤሊንግሃም “ሪያል ማድሪድ ለእኔ ፍጹም ክለብ ነው፤ እዚህ መኾን በጣም ያስደስተኛል” ሲል ለማርካ ተናግሯል። በማድሪድ ደስተኛ ነኝ እና በሚቀጥሉት 10 ወይም 15 ዓመታት በነጭ ማሊያ እጫወታለሁ ብዬ አስባለሁ” ብሏል።
✍️ራፊንሃ እና ኩባርሲ ለባርሴሎና ከአትሌቲኮ ጋር በሚደረገው ጨዋታ ለመሰለፍ ዝግጁ ሆነዋል። ሃንሲ ፍሊክ ሁለቱም ተጨዋቾች ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች እረፍት ከተሰጣቸው በኋላ ከአትሌቲኮ ጋር መጫወት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል።
✍️ጆአዎ ፊሊክስ የውሰት ጊዜውን ካጠናቀቀ በኋላ በዚህ የውድድር ዘመን በኤሲሚላን አይቆይም። ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ጀምሮ የነበረው ግልጽ ስሜት አሁን ተረጋግጧል፣ ጆአዎ ፊሊክስ ከሰኔ ወር ጀምሮ ወደ ቼልሲ እንደሚመለስ ይጠበቃል።
✍️ካርሎ አንቸሎቲ ቶኒ ሩዲገርን ዛሬ ምሽት አሳርፈው ዴቪድ አላባን በመሀል ተከላካይነት ሊያሰልፉ እንደሚችሉ ኤኤስ ዘግቧል።
✍️ሉዊስ ሱዋሬዝ “አያክስን ስለቅ ከሊቨርፑል እና ከቶተንሃም ጥያቄዎች ነበሩኝ ግን ሊቨርፑልን መረጥኩ ብሏል።
✍️ሃንሲ ፍሊክ ሉዊስ ዲያዝን በባርሴሎና እንደማይፈልጉት ማርካ ዘግቧል።
✍️ሩበን አሞሪም”ብሩኖ የማይተካ ነው። ለወደፊቱ የሚያስፈልገን አይነት ተጫዋች ነው” ብለዋል።
✍️ሩበን አሞሪም ኮቢ ማይኖ በስብስባቸው ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልገውን የአካል ብቃት እንደሌለው ተናግረዋል
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!