ባሕር ዳር፡ መጋቢት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል የስፖርቲንግ አጥቂ ቪክቶር ጂዮከሬስን ለማስፈረም ጥረት ማድረጉ ሲገለጽ ማንቸስተር ሲቲ በበኩሉ የኤሲ ሚላን አማካይ ቲጃኒ ሬይንደርስን የግሉ ለማድረግ ፍላጎት ማሳደሩ ታውቋል።
የአርሰናል አዲሱ የስፖርት ዳይሬክተር አንድሪያ በርታ የጂዮከሬስን አድናቂ መኾናቸው ተጫዋቹን ለማዘዋወር ይበልጥ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ነው የተገለጸው።
የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ውሉ ሲጠናቀቅ ወደ አያክስ ሊመለስ ይችላል የሚሉ ወሬዎች ከፍ ብለው እየተሰሙ ነው።
ኤቨርተን የሊቨርፑሉን ወጣት ተጫዋች ቤን ዶአክን በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም እቅድ ስለመኖሩም ተገልጿል።
ማንቸስተር ዩናይትድ የኢንትራክት ፍራንክፈርት አጥቂን ሁጎ ኢኪቲኬን ለማስፈረም እያደረገ ያለው ጥረት ጥሩ ነው የተባለ ሲኾን ተጫዋቹ የክለቡ ደጋፊ በመኾኑ ሊሳካ እንደሚችል ነው እየተገለጸ የሚገኘው።
የኢፕስዊች ታውን ሊቀ መንበር ማርክ አሽተን ስለ ሊያም ዴላፕ የውል ዝርዝር መግለጽ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።
ባየር ሙኒክ ቶማስ ሙለርን ለማቆየት እቅድ ባይኖረውም ተጫዋቹ ወደ ሜጀር ሊግ እግር ኳስ ክለቦች ሊያመራ ይችላል ተብሏል።
የዎልቭስ አጥቂ ማቲየስ ኩኛ ክለቡን ለመልቀቅ እያሰበ መኾኑን ፍንጭ ሰጥቷል።
የባየር ሌቨርኩሰን አሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ስማቸው ከሪያል ማድሪድ ጋር ቢገናኝም ከክለቡ ጋር ለመቆየት መወሰናቸውን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!