ባሕር ዳር፡ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሳውዝሃምፕተኑ ወጣት የመስመር ተጫዋች ታይለር ዲብሊንግ በማንቸስተር ሲቲ እና ቶትንሃም እየተፈለገ ነው። ሳውዝአፕተን የተጫዋቹ የመሸጫ ዋጋ 100 ሚሊዮን ፓውንድ መኾኑን አሳውቋል። እንግሊዛዊ ታዳጊ እያሳየ ያለው እንቅስቃሴ በትልልቅ ክለቦች አይን እንዲገባ አድርጎታል።
ኒውካስል ዩናይትድ የሊቨርፑሉን የመሐል ተከላካይ ጃሬል ኮንሳን ለማስፈረም 30 ሚሊዮን ፓውንድ ለማቅረብ መዘጋጀቱ ተገልጿል። በሌላ በኩል ኒውካስል በሊቨርፑል እና አርሰናል በጥብቅ ከሚፈለገው አሌክሳንደር ኢሳቅ ጋር እያደረገ የነበረውን የውል ማራዘም ድርድር አቋርጧል ተብሏል። ተጫዋቹ የመጀመሪያውን የድርድር ሂደት አልተቀበለም።
የበርንማውዝ የክለብ ኅላፊዎች በሚሎስ ኬርኬዝ እና አንቶይን ሴሜንዮ የወደፊት የክለቡ ቆይታ ዙሪያ ለመወሰን በዚህ ሳምንት ስብሰባ ያደርጋሉ። ተከላካዩ ኬርኬዝ እና የመስመር አጥቂው ሰሜንዮ በሊቨርፑል ክትትል ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው። የማንቸስተር ዩናይትድ የክንፍ ተጫዋች ጃዶን ሳንቾ ወደ ጀርመን ቡንደስሊጋ ለመመለስ ፍላጎት አሳይቷል፤ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ባየር ሌቨርኩሰንም ተጫዋቹን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።
ሳንቾ ንብረትነቱ የዩናትድ ቢኾንም አሁን በውሰት በቼልሲ እየተጫወተ ነው። ቼልሲ የበርንማውዙን ተከላካይ ዲን ሁይጀንን ለማስፈረም ከሪያል ማድሪድ ጋር ፉክክር ውስጥ እንዳለ ነው ቢቢሲ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ የዘገበው።
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን