በአፍሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ በርከት ያሉ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

0
186

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) እነዚህ ጨዋታዎች የአፍሪካ ሀገራት ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ያላቸውን ተስፋ የሚወስኑ ወሳኝ ጨዋታዎች ናቸው። የጨዋታዎቹ ውጤት በአፍሪካ እግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት እየተሰጣቸውም ናቸው።

ኢትዮጵያ በተደለደለችበት ምድብ አንድ ግብጽ ከሴራሊዮን ጋር ምሽት 4 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።በምድብ ሁለት ደግሞ ሱዳን ከደቡብ ሱዳን ጋር ነው 4 ሰዓት ጨዋታቸውን የሚያከናውኑት።በዚሁ ምድብ ሞሪታኒያ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር 6 ሰዓት የሚያደርጉት ሌላው ጨዋታ ነው።
ሴኔጋል ከቶጎ ጋርም በተመሳሳይ በዚሁ ምድብ ይጫዎታሉ።

በምድብ ሦስት ደግሞ ቤኒን ከደቡብ አፍሪካ ጋር ምሽት 1 ሰዓት ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት። በዚሁ ምድብ ናይጄሪያ ከዚምባብዌ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ይጫዎታሉ። ሩዋንዳ ከሌሶቶ ጋር የሚያደርጉት ሌላው የዚህ ምድብ ጨዋታ ይኾናል።

በምድብ አራት ከተደለደሉት ቡድኖች መካከል ደግሞ አንጎላ ከኬፕ ቨርዴ ጋር ምሽት 1 ሰዓት ሲጫዎቱ በዚሁ ምድብ ካሜሩን ከሊቢያ ጋር ምሽት 4 ሰዓት ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት።

በምድብ አምስት ደግሞ ሞሮኮ ከታንዛኒያ ጋር ምሽት 6:30 ይጫዎታሉ። በምድብ ስድስት ቡሩንዲ ከሲሼልስ ጋር 4 ሰዓት ሲጫዎቱ በምድብ ሰባት የተደለደሉት ዩጋንዳ ከጊኒ ጋር 1 ሰዓት ላይ ይጫዎታሉ።

ቦትስዋና ከሶማሊያ ጋር 4 ሰዓት ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት። በዚሁ ምድብ አልጄሪያ ከሞዛምቢክ ጋር 6 ሰዓት ይጫዎታሉ። በምድብ ዘጠኝ ደግሞ ኮሞሮስ ከቻድ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here