ኢትዮጵያ ጅቡቲን በሰፊ ጎል አሸነፈች።

0
163

ባሕር ዳር: መጋቢት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአፍሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በስታድ ቤን አህመድ ኤል አብዲ ስታዲየም ተካሂዶ ኢትዮጵያ ጅቡቲን 6 ለ 1 አሸንፋለች።

በረከት ደስታ እና አቡበከር ናስር እያንዳንዳቸው ሀትሪክ ሰርተዋል። በረከት በ19ኛው፣ በ52ኛው እና በ70ኛው ደቂቃ፣ አቡበከር ናስር ደግሞ በ34ኛው፣ በ37ኛው እና በ58ኛው ደቂቃ ነው ግቦችን ያስቆጠሩት።

የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድቡ ያላትን ነጥብ ስድስት ማድረስ ችላለች።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here