ባሕር ዳር: መጋቢት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጂቡቲ ጋር እኩለ ሌሊት ላይ ትጫወታለች።
ጨዋታው በሞሮኮ ስታድ ቤን አህመድ ኤል አብዲ ስታዲየም ነው የሚካሄድ።
ሁለቱም ቡድኖች በምድብ አንድ የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኛሉ። ዛሬ የሚያደርጉት የእርስ በእርስ ጨዋታም ነጥባቸውን ከፍ ለማድረግ የሚያግዝ ነው። በመኾኑም ጨዋታው ተጠባቂ ነው።
ዋሊያዎቹ ከቀናት በፊት በግብጽ 2 ለ 0 መሸነፋቸው ይታወሳል።
በሌሎች የአፍሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከምድብ 1 ጊኒ ቢሳው ከ ቡርኪናፋሶ፤ ከምድብ 5 ኮንጎ ከ ዛምቢያ፤ ምድብ 6 ኮትዲቯር ከ ጋምቢያ፤ ምድብ 8 ናሚቢያ ከ ኢኳቶሪያል ጊኒ፤ ላይቤሪያ ከሳኦቶሜ፤ ቱኒዚያ ከ ማላዊ ምድብ 9 መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ከ ማሊ፤ ማዳጋስካር ከ ጋና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በምሥጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!