ፈረንሳይ ከስፔን፣ ፖርቱጋል ከጀርመን ይገናኛሉ።

0
159

ባሕር ዳር: መጋቢት 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ፖርቹጋል እና ስፔን በኔሽንስ ሊግ ለግማሽ ፍጻሜ ደርሰዋል፡፡ በግማሽ ፍጻሜውም ጀርመን ከፖርቱጋል እና ፈረንሳይ ከስፔን ይገናኛሉ፡፡

ፈረንሳይ በክሮሽያ በመጀመሪያው ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋ ነበር። ትናንት ምሽት በተደረገው ጨዋታ ፈረንሳይ 2 ለ 0 አሸንፋለች። ፈረንሳይ በመለያ ምት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች።

ጀርመን እና ጣሊያንም የምሽቱን ጨዋታ ሦስት አቻ አጠናቅቀዋል። ጀርመን በደርሶ መልስ 5 ለ 4 በማሸነፍ ግምሽ ፍጻሜ ቦታዋን አረጋግጣለች። በዴንማርክ የተፈተነችው ፖርቱጋልም አራቱ ውስጥ ገብታለች። መደበኛ የጨዋታው ጊዜ በፖርቱጋል 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

የመጀመሪያውን ዙር ደግሞ ዴንማርክ 1ለ0 ረትታለች። አሸናፊውን ለመለየት ወደ ጭማሪ ደቂቃ ያመሩ ሲኾን ፖርቱጋል የማታ ማታ ድል ቀንቷታል። ስፔን ከኔዘርላንድ የተደረገው ሌላው አዝናኝ ጨዋታ ሦስት አቻ ተጠናቅቋል። በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በተመሳሳይ በአቻ ውጤት ነበር የተጠናቀቀው።

የምሽቱን ጨዋታ ስፔን በመለያ ምት አሸንፋ በቀጣይ ሰኔ ለሚካሄደው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ደርሳለች።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here