በዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ማን ከማን ይጫወታል?

0
157

ባሕር ዳር: መጋቢት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት አመሻሽ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ተካሂደዋል። የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚ ቡድኖችም ተለይተዋል። የስፔኑን ክለብ ሪያል ሶሲዳድን በሜዳው ኦልድትራፎርድ የጋበዘው ማንቸስተር ዩናይትድ 4ለ1 አሸንፏል።

አንበሉ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሀትሪክ ሲሰራ ዲያጎ ዳሎት ቀሪዋን ግብ አስቆጥሯል። ማንቸስተር ዩናይትድ ትናንት ማሸነፉን ተከትሎ በዩሮፓ ሊግ ያለመሸነፍ ጉዞውን አስቀጥሏል። ማንቸስተር ዩናይትድ በሩብ ፍጻሜው ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ጋር ይገናኛል።

በመጀመሪያው ጨዋታ ያጋጠመውን ሽንፈት ቀልብሶ ወደ ሩብ ፍጻሜው ያለፈው የእንግሊዙ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከ ጀርመኑ ኢንትራክት ፍራንክፈርት ጋር ተገናኝቷል። የጣሊያኑ ላዚዮ ደግሞ ከ ኖርዌዩ ቦዶ ጋር ይጫወታል።

የስኮትላንዱ ሬንጀርስ ከ ስፔኑ አትሌቲክ ቢባኦ ጋር ሲገናኝ በዩሮፓ ሊግ ብቻ ዋንጫ የማሸነፍ እድል ያለው ማንቸስተር ዩናይትድ ለውድድሩ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ይጠበቃል።

የዩሮፓ ሊግን ማሸነፍ የሚችል ከኾነ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መሳተፍ ይችላል።

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here