ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሪያል ሶሲዳድ የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረት ስቧል።

0
110

ባሕር ዳር: መጋቢት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዩሮፓ ሊግ ስምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ፡፡ ከዕለቱ ጨዋታዎችም ማንቸስተር ዩናይትድ እና ሪያል ሶሲዳድ የሚገናኙበት ጨዋታ ትኩረት አግኝቷል። በቅርቡ በፕሪምየር ሊጉ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች እና በኤፍኤ ካፕ በአቻ ውጤት ያጠናቀቀው እና ኢፕሲዊች ታውንን 3ለ2 የረታው ማንቸስተር ዩናይትድ በግብ ድርቅ ተመትቶ ታይቷል፡፡

ደካማ አቋሙ በየጨዋታዎቹ ጎልተው ከመውጣት ባለፈ ትንሽም ቢኾን መሻሻል ያላሳየው ማንቸስተር ዩናይትድ ዛሬ ከሚገጥመው ሪያል ሶሲዳድ ጋር ያለውን ጨዋታ ለማሽነፍ የአጥቂ መስመሩ ይበልጥ ተጠናክሮ መግባት ይጠበቅበታል፡፡ በቅርቡ ከሪያል ሶሲዳድ ጋር የተገናኘው ዩናይትድ 1ለ1 መለያየቱ እና በጨዋታው ይበልጥ ለጎል የቀረቡ ሙከራዎችን አለማድረጉ የዛሬውንም ጨዋታ የአጥቂ ክፍሉን አጠናክሮ ካልቀረበ የማሸነፍ ዕድሉ አስቸጋሪ ሊኾን እንደሚችል ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

በሌላ በኩል ሪያል ሶሲዳድ ባለፉት ጊዚያት በላሊጋው እና በዩሮፓ ሊግ እንድኹም በኮፓ ዴላሪ በቅርቡ ካደረጋቸው ጨዋታዎች ውስጥ አንዱን ብቻ ሲያሸንፍ ሦስቱን ጨዋታዎች በሽንፈት አጠናቅቋል፡፡ ሪያል ሶሲዳድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በቅርቡ በአውሮፓ ሊግ ያደረገውን ጨዋታ አቻ መለያየቱ ዛሬም በጨዋታው ጥሩ ተፎካካሪ ሊኾን እንደሚችል ነው የሚገመተው፡፡

ይኹን እንጅ ሪያል ሶሲዳድ የአጥቂ ክፍሉ ደካማ መኾኑ በዚህኛው ጨዋታ ተጠናክሮ መቅረብ ካልቻለ ግብ ለማስቆጠር እና ጨዋታውን በበላይነት ለማጠናቀቅ ሊቸገር እንደሚችል ነው እየተነገረ ያለው፡፡ ሁለቱ ክለቦች እስካኹን በቅርቡ ካደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች ውስጥ ሦስቱን በሪያል ሶሲዳድ ሜዳ ሲገናኙ ሁለቱን ጨዋታ ደግሞ በማንቸስተር ዩናይትድ ሜዳ አድርገዋል፡፡

በዚህም ሁለት ጊዜ አቻ ሲለያዩ ሁለት ጊዜ ማንቸስተር ዩናይትድ አሸንፏል። አንድ ጊዜ ደግሞ ሪያል ሶሲዳድ ማሸነፍ ችሏል፡፡ ጨዋታውም ምሽት 5:00 ይካሄዳል፡፡ ሌሎች ጨዋታዎችም ሲቀጥሉ የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ ከኖርዊ ቦዶ ጊልሚት፣ የጀርመኑ ኢንትራንት ፍራንክፈርት ከኔዘርላንዱ አያክስ፣ የጣሊያኑ ላዚዮ ከቸኩ ቪክቶሪያ ፕሌዝ፣ የስፔኑ አትሌቲክ ቤልባኦ ከጣሊያኑ ሮማ፣ የስኮትላንዱ ሬንጀርስ ከቱርኩ ፌነርባቼ፣ የፈረንሳዩ ኦሎምፒክ ሊዮን ከሮማኒያው ኤፍሲኤስቢ፣ የእንግሊዙ ቶተንሃም ሆትስፐር ከኔዘር ላንዱ አልካማር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here