ባሕር ዳር: መጋቢት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ22ኛ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ 9 ሰዓት ላይ መቻልን ከፋሲል ከነማ አገናኝቷል። በጨዋታውንም ፋሲል ከነማ 4ለ2 በኾነ ውጤት አሸንፏል።
በጨዋታው በ28 ኛው ደቂቃ አቤል ነጋሽ ባስቆጠራት ግብ መቻል መምራት ቢችልም በ42ኛው ደቂቃ ጌታነህ ከበደ ለፋሲል ከነማ አስቆጥሮ አቻ አድርጓል።
ከእረፍት መልስ ጥሩ የተንቀሳቀሰው ፋሲል ከነማ በ58ኛው ደቂቃ በጌታነህ ከበደ፣ 69ኛው ደቂቃ በቢኒያም ጌታቸው እና በ76ኛው ደቂቃ በምኞት ደበበ ግቦችን አስቆጥሯል። የመቻልን ሁለተኛ ግብ 90+8′ ፊሊሞን ገብረጻድቅ አስቆጥሮ ጨዋታው በፋሲል ከነማ 4ለ2 በኾነ ውጤት ተጠናቅቋል።
ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ27 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ጨዋታ ሲቀጥል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬዳዋ 12:00 ሰዓት ይጫወታሉ።
ፕሪምየርሊጉን ኢትዮጵያ መድን፣ ባሕርዳር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ ይዘው እየመሩ ይገኛሉ።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!