ሊቨርፑል ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሰናበተ።

0
152

ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአንፊልድ ሮድ የፈረንሳዩን ፒኤስጂን ያስተናገደው ሊቨርፑል በሜዳውና በደጋፊው ፊት ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል።

በመጀመሪያው ጨዋታ ወደ ፈረንሳይ አቅንቶ 1ለ0 አሸንፎ የተመለሰው ሊቨርፑል በሜዳው ውጤቱን ማስጠበቅ አልቻለም።

በሜዳው ተሸንፎ የነበረው ፒኤስጂ በአንፊልድ ሮድ 1ለ0 መርቷል። ሙሉ ዘጠና ደቂቃውም በፒኤስጂ 1ለ0 መሪነት ተጠናቅቋል። አሸናፊውን ለመየት ተጨማሪ 30 ደቂቃ ቢሰጥም ግብ ሳይቆጠርበት ደቂቃው ተጠናቅቋል። በመጨረሻም አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ፒኤስጂ ድል በማድረግ ወደ ሩብ ፍጻሜው መግባቱን አረጋግጧል።

በሌሎች ጨዋታዎች ባየርንሙኒክ ባየርሊቨርኩሰንን፣ ኢንተር ሚላን ፌኖሮድን፣ ባርሴሎና ቤኔፊካም አሸንፈው ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here