22ኛው የባሕል ስፖርት ውድድር እና 18ኛው የባሕል ስፖርት ፌስቲቫል እንደቀጠለ ነው።

0
116

ባሕር ዳር: መጋቢት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሦስተኛ ቀኑን በያዘው 22ኛው የባሕል ስፖርት ውድድር እና 18ኛው የባሕል ስፖርት ፌስቲቫል ላይ የገና ጨዋታ እና የትግል ስፖርት ዛሬ መካሄድ ጀምረዋል። በገና ጨዋታ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል። የአማራ ክልል ድሬድዋን 2 ለ 0 አሽንፏል። ኦሮሚያ 1 ለ 0 ሲዳማን እና አዲስ አበባ 2 ለ 0 ደቡብ ኢትዮጵያን አሸንፈዋል።

በትግል ከ48 እስከ 52 ኪሎ ግራም ዘርፍ በሁለቱም ፆታ ውድድሮች ተደርገዋል። በተመሳሳይ በወንዶች ከ53 እስከ 57 ኪሎ ግራም ውድድሮች ተከናውነዋል። ትግል ወንድ ከ63 እስከ 67 ኪሎ ግራም አማራ ክልል የአፋርን ተወዳዳሪ አሸንፏል።

በ48 እስከ 52 ኪሎ ግራም ባለው አማራ ክልል ደቡብ ኢትዮጵያን አሸንፏል። በሴቶች ውድድር ከ48 እስከ 52 ኪሎ ግራም ባለው የአማራ ክልል ጋምቤላን አሸንፏል።

ቡብ የወንዶች የጨዋታ ውጤትን በተመለከተ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 1ለ 1 ከድሬዳዋ ፤ ኦሮሚያ 1 ለ 1 ከአማራ ፤ አዲስ አበባ 2 ለ1 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ደቡብ ኢትዮጵያ 2- ለ 0 ከአፋር ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ቡብ የሴቶች የጨዋታ ውጤትን በተመለከተ ደግሞ ድሬዳዋ 2-0 ሲዳማ፤ አማራ 2-0 ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ ኦሮሚያ 1-1 ደቡብ ኢትዮጵያ እና አዲስአበባ 2-0 ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ውጤቶች የተመዘገቡ ኾነዋል።

ባለ 12 ጉድጓድ ገበጣ የወንዶች ጨዋታ ውጤት ደግሞ ኦሮሚያ 2-0 ደቡብ ኢትዮጵያ፤ አማራ 2-0 ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፤ አዲስ አበባ 2-0 ሲዳማ፤ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 2-0 ድሬዳዋ ኾነው ተመዝግበዋል።

ባለ 12 ጉድጓድ የሴቶች የገበጣ ጨዋታ ውጤትን በተመለከተ አዲስ አበባ 2-0 ሲዳማ፤ ኦሮሚያ 2-0 ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ አማራ 2-0 ሐረሪ፤ ድሬዳዋ 2-0 ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሌሎች የተመዘገቡ ነጥቦች ናቸው።

በ22ኛው የባሕል ስፖርት ውድድር እና 18ኛው የባሕል ስፖርት ፌስቲቫል በከሰዓት መርሐ ግብሩ የባሕል ፌስቲቫል ትርዒትም ተከናውኗል።

በመረሐ ግብሩ መሠረት ኦሮሚያ እና የአማራ ክልል እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ባሕላቸውን እና እሴቶቻቸውን ለዳኞች አቅርበዋል።

ዘጋቢ: ታሪኩ አይኔዋ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here