ባሕር ዳር: መጋቢት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለ2026 የዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታውን እያከናወነ የሚገኝው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ አምስተኛ እና ስድተኛ ጨዋታውን በቅርቡ ያደርጋል።
ምድብ አንድ ላይ የተደለደሉት ዋልያዎቹ ቀጣዩን ጨዋታቸውን ከግብጽ እና ጅቡቲ ጋር ያደርጋሉ።
ከግብጽ ጋር መጋቢት 12 በላውቢ ዛውሊ ስታድየም ይደረጋል። ከጅቡቲ ጋር የሚደረገው ጨዋታ ደግሞ በሞሮኮ መጋቢት 15 ቀን ኤል ጀዲዳ ኤል አብዲ ስታዲየም እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አሳውቋል።
ተጫዋቾቹ ከመጋቢት አራት ጀምሮ በቀጣይ በሚገለጽ ሆቴል በመሰባሰብ ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!