ባሕር ዳር: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች መልስ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ። ስምንት የመጀመሪያ ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ናቸው ዛሬ የሚደረጉት።
ከጨዋታዎቹ መካከል ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ የስፔኑ ሪያል ሶሴዳድን የሚያገኝበት ጨዋታ ጥሩ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ተጠብቋል።
ዩናይትድ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የቁልቁለት ጉዞ ላይ ቢኾንም በዩሮፓ ሊጉ ግን እስካኹን አልተሸነፈም። ክለቡ ብቸኛው የዋንጫ ተስፋውም ይሄ ውድድር ነው።
አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም ከጨዋታው በፊት በሰጡት ሃሳብ የዩሮፓ ሊግን ማሸነፍ በክለቡ ብዙ ነገሮችን ይቀይራል ብለዋል። ነገር ግን በክለቡ ቆይታቸው ላይ የሚመዘገበው ውጤት ለውጥ እንደማያመጣ አረጋግጠዋል።
አሠልጣኙ ሀሪ ማጉየር እና ማኑኤል ኡጋርቴ በመጠነኛ ጉዳት ከዛሬው ጨዋታ ውጭ መኾናቸውንም አሳውቀዋል።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ምሽት 2:45 ይጀምራል።
ኤዜድ አልካማር ከቶትንሃም፣ ፌነርባቼ ከሬንጀርስ፣ አያክስ ከፍራንክፈርት፣ ሮማ ከክለብ አትሌቲክ፣ ፍሲቢ ከሊዮን፣ ቦዶ ከኦሎምፒያኮስ እና ፕለዝን ከላዚዮ ይጫወታሉ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!