ማድሪድ “ደርቢ” በአውሮፖ ሻምፒዮንስ ሊግ ምሽት ይጠበቃል።

0
108

ባሕር ዳር: የካቲት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ቦታን ለማግኘት ዛሬ እና ነገ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ዛሬ ምሽት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ከጨዋታዎቹ መካከል የማድሪድ ክለቦች የእርስ በእርስ ግጥሚያ ትኩረት ስቧል። የከተማ ተቀናቃኞቹ በስፔን ላሊጋ በተቀራራቢ ብቃት ላይ ይገኛሉ።

26 ሳምንታትን በተጓዘው የስፔን ላሊጋ አትሌቲኮ ማድሪድ በ56 ነጥብ በባርሴሎና በአንድ ነጥብ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሪያል ማድሪድ ደግሞ ከዛሬ ተጋጣሚው በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱ ክለቦች በቅርብ ያደረጓቸው ሦስት ጨዋታዎች በተመሳሳይ አንድ አቻ የተጠናቀቁ ናቸው።

ቡድኖቹ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ነው ዛሬ በሪያል ማድሪድ ሜዳ የሚያደርጉት።

በሌሎች የምሽት ጨዋታዎች አርሰናል ወደ ኔዘርላንድ ተጉዞ ከፒኤስቪ ጋር ይጫወታል። ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከሊል፣ ክለብ ብራግ ከአስቶን ቪላ የሚጫወቱ ይኾናል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here