ባሕር ዳር: የካቲት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ተጋጣሚዎችን ቅዳሜ እና እሑድ በተደረጉ ጨዋታዎች ለይቷል።
በዚህ መሠረት ማንቸስተር ሲቲ፣ ፉልሃም፣ በርንማውዝ፣ክርስቲያል ፓላስ፣ ብራይተን፣ አስቶን ቪላ እና ፕሪስቶን የሩብ ፍጻሜ ቦታቸውን ማረጋገጥ ችለዋል። ኖቲንግሃም እና ኢፕሲዎች ደግሞ ዛሬ በሚያደርጉት ጨዋታ አንዳቸው አላፊ ይኾናሉ።
በቀጣይ ማንቸስተር ሲቲ ከበርንማውዝ፣ ፉልሃም ከክርስቲያል ፓላስ፣ አስቶን ቪላ ከፕሪስቶን እንዲኹም ብራይተን ከኢፕሲዎች እና ኖቲንግሃም አሸናፊ ጋር በሩብ ፍጻሜ የሚጫወቱ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!