የጣና ሞገዶቹ ከማራኪ ጨዋታ ጋር በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፉ።

0
150

ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ20ኛ ሳምንት የኢትዮጽያ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ባሕርዳር ከተማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አገናኝቶ በባሕርዳር ከተማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። በጨዋታው የመሪነት ቅድሚያውን በ14 ኛው ደቂቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተገኑ ተሾመ አማካኝነት ወስደዋል። ባሕር ዳር ከተማ ደግሞ አቻ የሚያደርገውን ግብ በ39 ደቂቃ መሳይ አገኘሁ አግኝቷል።

ፍጹም የጨዋታ የበላይነት የነበራቸው የጣና ሞገዶቹ በ61ኛው፣ በ83ኛው እና በ85ኛው ደቂቃ ሦስት ጎሎችን ወንድወሰን በለጠ አስቆጥሮ ሀትሪክ በመሥራት ጨዋታው ፍጻሜውን አግኝቷል። ባሕር ዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 4ለ1 በኾነ ውጤትም ማሸነፍ ችሏል። ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ ደረጃቸውን ወደ ሦስተኛ አሻሽለው የፕሪሚየርሊጉ ተፎካካሪ መኾናቸውን አረጋግጠዋል።

በሌላኛው የ20ኛ ሳምንት የኢትዮጽያ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታዎች ድሬዳዋ ከተማ እና መቻል ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here