ባሕር ዳር: የካቲት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ 0 ለ 0 በኾነ አቻ ውጤት አጠናቅቋል። በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኢፕስዊች ታውን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 2 በኾነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ሀሪ ማጓየር፣ ዴሊት እና ሞርሲ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኢፕስዊች ጃደን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለት ጎሎች አስቆጥሯል። ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ በኤርሊንግ ሀላንድ ግብ 1 ለ 0 በኾነ ጠባብ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።
የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ 20ኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።
በሌላ ጨዋታ ብሬንትፎርድ ከኤቨርተን ጋር 1 ለ 1 በኾነ የአቻ ውጤት ተለያይቷል።
በታዘብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!