የመላው ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ስፖርታዊ ውድድር ተጀመረ።

0
131

ጎንደር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዘጠነኛው የመላው ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ስፖርታዊ ውድድር በላይ አርማጭሆ ወረዳ አስተናጋጅነት በትክል ድንጋይ ከተማ ተጀምሯል። በዚህ ውድድር 13 ወረዳዎች እና ሁለት ከተማ አሥተዳደሮች ይሳተፋሉ። ውድድሩ በ10 የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ ሲኾን ከ750 በላይ ስፖርተኞች ይሳተፋሉ።

የየወረዳው ተሳታፊ ቡድኖች ለውድድሩ ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርጉ እንደቆዩ ገልጸዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ድግስ መለሰ የውድድሩ ዋና ዓላማ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት፣ የአካባቢውን ጸጋ ማስተዋወቅ እና አብሮነትን ማጠናከር መኾኑን ተናግረዋል።

የላይ አርማጭሆ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አስረሳው ደሴ ስፖርት ወንድማማችነትን ከፍ እንደሚያደርግ እና ለውድድር የሚመጡ እንግዶችም ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ የወረዳው አምባሳደር እንደሚኾኑ ገልጸዋል። ውድድሩ ለ12 ቀናት በትክል ድንጋይ ከተማ ቀጥሎ ይካሄዳል።

ዘጋቢ፦ ዳንኤል ወርቄ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here