ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጃፓን ኦሳካ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በጃፓን ኦሳካ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቅቀዋል።
👉በወንዶች ማራቶን ውድድር
አትሌት ይሁንልኝ አዳነ የቦታውን ሰዓት በማሻሻል እና የራሱን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ በአንደኝነት አጠናቋል።
አትሌት ይሁንልኝ ርቀቱን 2:05:37 በኾነ ሰዓት በመግባት ነው ያሸፈው።
👉በሴቶች ማራቶን ውድድር
አትሌት ዋጋነሽ መካሻ 2:26:33 በኾነ ሰዓት በመግባት በቀዳሚነት አጠናቃለች ።
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በሜክሲኮ ጓዳላሀራ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ታዱ አባተ 62:02 በመግባት አሸንፏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!