ሌሲስተር ሲቲ ከወራጅ ቀጣናው ለመውጣት ይጫወታል።

0
129

ባሕር ዳር: የካቲት 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ምሽት አንድ ጨዋታ ይደረጋል። ሌሲስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን በኪንግ ፓወር ስታዲየም ያስተናግዳል። ጨዋታው ምሽት 5:00 ላይ ይጀምራል።
ሁለቱ ቡድኖች ባደረጓቸው ያለፉት አምስት የእርስ በእርስ ጨዋታዎች ሌሲስተር ሲቲ ሁለቱን በማሸነፍ የበላይነት አለው። ብሬንትፎርድ ደግሞ አንድ ጨዋታ ብቻ ነው ያሸነፈው። ሁለት ጨዋታዎችን ደግሞ በአቻ ውጤት አጠናቅቀዋል።
ሌሲስተር ሲቲ ዛሬ የቀኝ መስመር ተከላካዩን ጀምስ ጀስቲን በጉዳት ምክንያት ላያሰልፈው ይችላል ተብሏል። ነገርግን ለቡድኑ አዎንታዊው ዜና ዎዮ ኩሊባሊ ወደ ሜዳ መመለሱ ነው።
ብሬንትፎርድ በበኩሉ አምስት ተጫዋቾችን በጉዳት ምክንያት እንደማያሰልፍ አስታውቋል። አሮን ሂኬይ፣ ሪኮ ሄነሪይ፣ ጆሹዋ ዳሲልቫ፣ ጉስታቮ ኑኔስ እና ኢጎር ቲያጎ ናቸው በጨዋታው የማይሰለፉት።
ሌሲስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ 25 ጨዋታዎችን አድርጎ 17 ነጥብ ብቻ በመያዝ በወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛል። የዛሬው ጨዋታ ከወራጅ ቀጣናው ለመውጣት አስፈላጊ ነው። ማሸነፍ ከቻሉ ወልቪስ እስኪጫወት ድረስ ከወራጅ ቀጣናው የሚወጡበት እልድ አለ።
ብሬንትፎርድ በበኩሉ 34 ነጥብ ይዞ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ደረጃውን ያሻሽላል።
ጨዋታውን ቶኒ ሃሪንግተን በዳኝነት ይመራሉ ተብሏል።
የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ሊቨርፑል እየመራ ነው። አርሰናል እና ኖቲንግሃም ፎሬስት ደግሞ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ኾነው ይከተሉታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here