“የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚተዳደርበትን ደንብ የክልሉ መንግሥት አውጥቷል” የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

0
134

ባሕር ዳር: የካቲት 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማዕከል የአደረጃጀት መዋቅር ጥናት እና ረቂቅ የአሠራር መመሪያዎች ዝግጅት ለማስተቸት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በባሕር ዳር ከተማ እየተመከረ ነው። የክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እና የስታዲየሙ የቦርድ ሠብሣቢ እርዚቅ ኢሳ ስታዲየሙን የሚያሥተዳድር ቦርድ እንደተቋቋመለት ተናግረዋል።

ቦርዱ የማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራልም ብለዋል። ስታዲየሙ የካፍ እና የፊፋን መስፈርት ሊያሟላ በሚችል መንገድ እየተገነባ ነው፤ አፈጻጸሙም ከ83 በመቶ በላይ ኾኗል ነው ያሉት። የክልሉ መንግሥት ስታዲየሙ የሚተዳደርበት ደንብ ማውጣቱንም ኀላፊው ተናግረዋል። በደንቡ ውስጥ ቦርድ እና የሠራተኛ መዋቅር እንደሚዘረጋለት ተቀምጧል ብለዋል።

በስታዲየሙ ውስጥ በርካታ ሱቆች፣ የጂም፣ የዋና፣ የስፖርት ትጥቅ መሸጫ ቦታዎች፣ ዘመናዊ ካፍቴሪያዎች እንዲሁም 10 የፋስት ፉድ መሸጫዎች ስላሉት ገቢ አመንጭቶ ራሱን እንዲያሥተዳድር ይደረጋል ነው ያሉት። በገቢውም ቴክኖሎጂውን እንዲያዘምንበት ኾኖ እየተሠራ መኾኑን አቶ እርዚቅ ተናግረዋል።
የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም 42 ሄክታር መሬት ይዞታ ያለው ሲኾን በወንበር 52ሺህ ተመልካች የመያዝ አቅም አለው።

ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here