ሊቨርፑል ወደ ቪላ ፓርክ ተጉዞ ይጫወታል።

0
229

ባሕር ዳር: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ዛሬ ሲቀጥል ሊቨርፑል ከአስቶንቪላ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡ ከ25 ጨዋታዎች 18 በማሸነፍ እና 6 ጨዋታዎችን አቻ ወጥቶ አንድ ጊዜ ብቻ ተሸንፎ በ60 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው ሊቨርፑል።

አስቶንቪላ ደግሞ 25 ጨዋታዎችን በፕሪምየር ሊጉ አድርጋል፤ 10 ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ ሰባት ጨዋታዎችን ደግሞ ተሸንፏል፤ በስምንት ጨዋታዎችን ደግሞ አቻ ተለያይቷል፡፡ አስቶንቪላዎቹ በደረጃ ሰንጠረዡ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጡት፡፡ በዛሬው ጨዋታ ካላቸው ወቅታዊ አቋም አንጻር ሊቨርፑሎች ሊከብዷቸው እንደሚችሉ ነው የሚገለጸው፡፡

ሁለቱ ቡድኖች 203 ጊዜ ሜዳ ላይ ተገናኝተዋል፤ ሊቨርፑል 102 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነት አለው። 59 ጊዜ አስቶንቪላዎች ድል ቀንቷቸዋል፤ 42 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ የተለያዩባቸው ናቸው፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here