ሪያል ማድሪድ ከማንቸስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው!

0
184

ባሕር ዳር: የካቲት 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዛሬ አራት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ ከእነዚህ ጨዋታዎች ውስጥ ሪያል ማድሪድ ከማንቸስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡ ሪያል ማድሪዶች በቅርብ ጊዜ ያደረጓቸውን አምስት ጨዋታዎች ስናይ አንድ ጊዜ ተሸንፈው ሁለት ጊዜ አቻ በመውጣት እና ሁለት ጊዜ በማሸነፍ የተሻለ አቋም ላይ ይገኛሉ፡፡

በማንቸስተር ሲቲ በኩል ሁለት ጊዜ ሽንፈትን በማስተናገድ እና ሦስት ጨዋታዎችን ደግሞ በማሸነፍ ጥሩ መሻሻል ላይ ነው። ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን 16 ጊዜ ተገናኝተዋል። አምስት ጊዜ ሲቲ ሲያሸንፍ ስድስት ጊዜ ደግሞ ማድሪድ በማሸነፍ የተሻለ ነው፡፡ አምስት ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ከሜዳው ውጭ ሲቲን ማሸነፉ ይታወሳል። ጨዋታው ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡ በሌላ ጨዋታ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ምሽት 2፡45 ጨዋታቸውን ሲያደርጉ፣ ፒኤስጂ ከብሬስት እና ፒኤስቪ ከጁቬንቱስ ደግሞ ምሽት 5 ሰዓት ይጫወታሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here